ሰበርመ ልስ: ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለደቡብ ክልል ምክር ቤት!!

# ሰበርመ ልስ: ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለደቡብ ክልል ምክር ቤት!! ይነበብ ሼር ይደረግ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሲዳማ ውስጥ ስለሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆችና ስለ ሀዋሳ ከተማ የወደ ፍት ሁኔታ የደቡብ ክልል የህግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ ብሎ ላለው እነ መልስ አለኝ። በመጀመርያ በሲዳማ ክልል ውስጥ ስለሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች የሚከተለውን እላለሁ።የሲዳማ ብሔር ክልል የሚሆንበት ማለትም ህዝቤ ውሳኔ /ድምፅ ልየታ/ የሚደረግበት ቀን ህዳር 3/2012 ዓ.ም እንደሚሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ሀምሌ 23/12/11 ዓ.ም ተገልፃል።

ይሁንና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚያገባውና በህግ ከተሰጠው ስልጣን ውጭ ጣልቃ እየገባና በህዝቡ መካከል ልዩነትን፣መከፋፈልን የሚያመጣ ስራ ለመስራትና ለማከናወን ሽር ጉድ እያለ መሆኑ ግልፅ ነው። በመጀመርያ በሲዳማ ውስጥ ስለሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች አንዳንድ ሀሳቦች መግለጥ እፈልጋለሁ።

የሲዳማ ብሄር ከዘመነ መሳፍንት ጀምረው ከብዙ ብሄር ብሄረስቦች ጋር በፍቅር በጋራ ተቻችለውና ከተባብረው ተዋድደው ተዋልደው በአንድነት ስኖር በህግ ሳይሆን በሲዳማ ህዝብ መልካምነት በአቃፊነቱ ነው። ስጀምር ሲዳማ ብሄር ለይተው አያውቅም። ልዩነት አሁን ሊፈጠር እየተሞከረ ያለበት አካሄድ ነው እየሆነ ያለው። እንዲህ አይነቱ አካሄድ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባ በሲዳማ ውስጥ ስለሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች የሚጠብቅ የህግ ማዕቀፍ ይረቀቅ። ሲዳማ ክልል ስሆን ይቀየራል።ሌላውን ይገፋል በሚል የሙት አስተሳሰብ እየቆሶቆሱ በሲዳማና በሲዳማ ውስጥ የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች መሃል የማይበርድ ፀብ ለመዝራት ካለሆነ በቀር ሌላ ምንም አላማ የለውም። ህዝቡ ያላሰበውን እያሳሰባችሁ ችግር ባትፈጥሩ መልካም ነው።

ሲዳማ ክልል ከመሆኑ በፊትም ሲዳማ ነው ክልል ስሆን ደግሞ የሚቀየር ባህል ትውፍት የለውም። ሲዳማ ሌላውን የሚያከብረው ህግን ፈርተው ሳይሆን ፈጣርን ባህሉንና እያንዳንዱ ሰው ህሊናውን ፈርተው ነው በፍቅር ተከባብረው ስኖር የነበው። ሲዳማ በደቡብ ክልል ስር በነበር ጊዜ ሌላውን ያልገፋ።አሁን ማንነቱ በተከበረለትና ብርሃን በበራለት ሰአት ይበልጥ ሌላውን ያቅፋል እንጂ አይገፋም። ስለዚህ በኦሮሚያ በአማራ በትግራይ በሶማሌ ክልሎች የለለ ህግ በሲዳማ ክልል የሚኖርበት አግባብ አይፈጠርም አይኖርም። በሌሎች ክልሎች የሌላ ብሄር ተወላጆች እንደሚኖሩበት ሁሉ በሲዳማ ከዛ በላይ ደልተዋቸው ይኖራሉ።

ለዚህ ማረጋገጫ ሊሆን የሚችለው ከራሳቸው በሲዳማ ውስጥ የሚኖሩትን የሌላ ብሄር ተወላጆች መጠየቁ ይጠቅማል። ለምን ነገ የሚኖሩበት ክልል ስለሆነ በህግ ሳይሆን በፍቅር ተቻችለው በአንድነት መኖርን ይመርጣሉ። ከመረጡ ህግ ወረቀት ነው ምንም አቅም የለውም ሊጎዱ ይችላሉ ልዩነት ከተፈጠረ። ስለዚህ ጉዳይ ላይ ምርጫ ቦርድ ልዩነት ፈጥረው በሲዳማ ውስጥ የሚኖሩ ብሄሮች ላይ መጨረሻ የለለው ጉዳት ባያስቀምጥ መልካም ነው። እነርሱም ብሆኑ ብልጥ መሆን ይጠብቅባቸዋል። የሲዳማ ህዝብ ከብዙ ብሄር ተወላጆች ጋር በፍቅር ተከባብረው ለዘላለም ይኖራል እንጂ ህግን ፈርተው አይኖርም። ሲዳማ ክልል ስሆን ይበልጥ ሌሎቹን ያቅፋል ምንም የህግ ማዕቀፍ አያስፈልግም።

ህግ ማርቀቅ ማለት በሲዳማ ውስጥ የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ችግር ውስጥ እንድገቡ ከማድረግ ውጭ በሲዳማ ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ አያሳድርም። ይበልጥ ሲዳማ ሌሎቹን ለይተው እንዲያውቅ ይረዳዋል። ምርጫ ና ደቡብ ክልል ህግ የሚያወጣ ከሆነ ሁሉንም ቆጥረው ይዟቸው ይሄዳል እንጂ በሲዳማ ምድር የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች ብሎ በልዩነት ማስቀመጥ በፍፁም አይልቻም።

#የኢትዮጽያ ብሔራዊ ስለ ሀዋሳ ከተማ ብሎ ላነሳው ሀሳብ እነ ከበቅም በላይ መልስ አለኝ። ሌላው የሀዋሳ ከተማ ጉዳይ ነው
ሀዋሳ በ1952 ዓ.ም የተቆረቆረች ውቧ የሀገራች የከተሞች ተምሳሌት ማራክ ከተማ ናት ሀዋሳ። ይህ ከተማ ከተቆረቆረችበት ቀን አንስተው የሲዳማ አስተዳደር ዋና ከተማ በመሆን ስታገለግል እየኖረች ያለች ከተማ ናት። አሁን ሲዳማ ክልል ስለሆን የሚፈጠር ሌላ አድስ ታሪክ የለም አይኖምም። ምክንያቱም ሀዋሳ ተጭና የመጣች ከተማ አይደለችም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በእናንተ ስህተት ለዘመናት በአንድነት የኖረ ህዝብ እንዳከፋፈል።

ትንሽ ስለሀዋሳ

“”Hawaasi Quchuma””
Hawaasa <<Baxxillu Quchuma>>
ሀዋሳ <<የፍቅር ከተማ>>
Hawaasa is a city in the Great Rift Valley of Centeral Ethiopia
(ዘገባ አንድ) ስለ ሀዋሳ
ስምጥ ሸለቆ በአራት ተፋሰሶች ተከፍለዋል።
እነርሱም ዝዋይ፣ሀዋሳ፣ሻላ፣አባያና ጫሞ እንዲሁም ጨው ባህር ተብሎ ይጠራሉ።

በእነዚህ ተፋሰሶች አከባቢ 12.6 ሚሊዩን ህዝብ ይኖራሉ። 13 ከመቶው በከተማ 87 ከመቶው ደግሞ በገጠር የሚገኙ ናቸው። ይህ ተፋሰስ 53 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ይሸፍናል።

ከተማ የሚትገኘው በኢትዮጵያ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከአድስ አበባ በ275 ኪሜ ርቀት ላይ ነው የሚትገኘው።

ከተማዋ በምእራብ እና በሰሜን ምእራብ አቅጣጫ በሀዋሳ ሓይቅ፣በምስራቅና በደቡብ ምስራቅ በጨለልቃ ራግራጋማ መሬት ፣በሰሜን በጥቁር ውሃ እንዲሁም በደቡብ አቅጣጫ በአላሙራ ተራራ ትዋሰናለች። አስተሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ070 03′ በሰሜን ላቲትውድ በ300 25 በምስራቅ ሎንግቲውድ ነው።

በስምጥ ሸለቆ ሕይቆች ተፋሰሶች ውስጥ ከ500 በላይ የአዕዋፋ ዝርያዎች የሚገኙበት፣አያሌ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚካሄድበት እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የቱርስት ፍሰት የሚስተዋልበት ክልል ነው ሲዳማ።

በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኘው የዝዋይ ሕይቅ ደግሞ 400 ኪሜ ስኩዌር ይሸፍናል። ከተማዋ በ1952 ዓ.ም በራስ መንገሻ ስዩም በአጼ ሃይለስላሴ ፈቃድ የተቆረቆረች ሲሆን፣የዛሬውን ቅርስ ከመያዟ በፍት ስፍራው ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነ የዱር እንስሳት መኖርያ ነበረ።

የሀዋሳ ከተማ ከመመሰረቷ በፍት በስፍራው ሲዳማ በአርብቶ አደርነት ይኖሩ ነበረ ።በሂደት በ1953 ዓ.ም 400 የሲዳማ አከባቢ ጡረተኛ ወታደሮችና ቤትሰቦቻቸው በስፍራው እንዲሰፍሩ በመደረጉ ለከተማዋ መቆርቆር መመሰረት ምክንያት ሆነዋል። ከተማዋ ከ1952 እስከ 1960 ዓ.ም የሀዌላ ወረዳ ርዕሰ ከተማና 1960 አከባቢ ቀድሞው የነበረው የሲዳማ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ በመሆን ያግለገለች ሲሆን 1954 ዓ.ም በማዜጋጃ ቤትነት ተመዝግባለች።

“ሀዋሳ” የሚለው የከተማዋ ስያሜ ከሀዋሳ ሕይቅ ስም የተወሰደ ሲሆን ሀዋሳ ማለት በSidaamu Afoo(በሲዳምኛ ቋንቋ) ሰፊ የውሃ አካል ማለት ነው። ከተማዋ ከመመሰረቷ በፍት ስፍራው “አዳሬ”በመባል የሚታወቅ ሲሆን ትርጉሙም በሲዳሙ አፎ(በሲዳሚኛ)የከብቶች መዋያ ማለት ነው።

ሰፊ የግጦሽ መሬትና አመቱን ሙሉ የሚገኝ ብዙ የውሃ ሀብት መኖሩ በደጋ አከባቢ የሚኖሩ ገበሬዎችንና በቆላ አከባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደሮችን ወደ አከባቢው ስቧል።ሀዋሳ በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዲዋ ስሆን በስሯ የከተማ አስተዳደር፣8 ክፍለ ከተሞች ይዛለች።

የክ/ከተሞቹ ስም አድስ ከተማ፣ሃይቅ ዳር፣ሀዌላ ቱላ፣ምስራቅ ፣ታቦር፣ባህል አዳራሽ፣መሃል፣መናኽርያ። ናቸው። የከተማዋ የመጀመርያው ማስተር ፕላን የተዘጋጀላት በቀድሞው ሀገር ውስጥ ጉዳይ ምንስቴር ነው።ይህ ፕላን የከተማዋን ዕድገት እስከ 1980 ዓ.ም የመራ ስሆን አድስ ማስተር ፕላን በ1986 ዓ.ም በብሄራዊ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ተዘጋጅቶላታል።

በአሁኑ ግዜ እያገለገለ ያለው ፕላን የተቀናጄ የከተሞች ፕላን የሚባል ስሆን በ1998 ዓ.ም በፌዴራል ከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት የተዘጋጄ ነው።በ2010 ዓ.ም መጨረሻ አከባቢ አድስ የከተማ ማስፋፍያ ተብሎ የተዘጋጀላትን አድስ ማስተር ፕላን በሲዳማ አርሶ አደሮች ላይ ጉዳት ያመጣል በሚል የሲዳማ ህዝብና ኤጄቶ አግልገሎት እንዳይሰጥ አድርጎታል።

ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተገናኘ ማለትም በሀዋሳ አለ የሚባሉ መሰረተ ልማቶች ሰበብ በሲዳማ ህዝብ ላይ ይሄ ነው የማይባል ጉዳት ያስከተሉ ናቸው። የሀዋሳ እንዱስትር ፓርክ የሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ዩንቨርስቲ ወዘተ ስገነቡ በቦታው ላይ የነበሩ የሲዳማ አርሶ አደሮች ቤት ንብረታቸውን አጥተዋል። ከሜዳ ወጥተዋል ስለዚህ ለእነዚህ ተፈናቃዮች በቂ ካሳ እንጂ ስለ ሀዋሳ የወደ ፍት እጣ ፋንታ የሚታይበት አግባብ የለውም።

ስለሆነም ብዙም ማብራራት ሳያስፈልግ ሀዋሳ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሆና ትቀጥላለች። ሀዋሳ በሲዳማ ደምና አንጥንት የታጠረች ውቧ ከተማችን ስለሆነች ማንም መጥተው ይኖርባታል ሀብት አፍርቶ በልፅገው ይከብርባታል። ሀዋሳ አዎን የሚታስጎጅ ውብ ከተማ ናት እንኳን የሰው ልጆች ከብቶች ይወዷታል። ሀዋሳን ምርጫው ያደረገ ያለ አንዳች ስጋት በሰላም ይኖርበታል።

ስለዚህ ወገኖቼ በሲዳማ ውስጥ ስለሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆችና ስለ ሀዋሳ ከተማ የወደ ፍት እጣ ፋንታ ሁኔታ ምንም አይነት ስጋት ሳይገባችሁ ያለ ልዩነት ከሰፊው ህዝብ ሲዳማ ጋር በፍቅር የሚኖሩ መሆናችሁን እየገለፅኩ መንግስት በህዝብ ውስጥ ያልነበረ ገና አድስ ችግር ባይቀሰቅስ መልካም ነው።

በሲዳማ ውስጥ የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ሲዳማ ናቸው ንብረታቸውም የሲዳማ ነው። ከሲዳማ ተወላጆች እኩል መብታቸው የተከበረ ነው። ሀዋሳ ደግሞ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መዲና።

መልካም ተግባር ነው።
መስከረም 26/2012 ዓ.ም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ። አሁን ካለሁበት!
ሰላም ለኢትዮጵያ #ሼር

Via: Buurisame Sharro Albirra


# ነፃ ፖለቲካ እናራምድ#
ሰሞኑን የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ብሔርተኝነትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተስማምተው አንድ ስምምነት ተፈራርመዋል:: በዚሁ ሰሞን ደግሞ ኦዴፓ እሮሞነቱን እርግፍ አድርጎ ትቶ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ውሁድ ፓርቲ እንደሚመሰርት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወስኗል:: ኦዴፓ ኦሮሞነቱን አውልቆ ጥሎ ማንንም ለማገልገል ቢወስን መብቱ ነው : ነገር ግን በኦሮሞ ስም ይተረከበውን የመንግሥት ኃላፊነትና ከኦሮሞ የሰበሰበውን ሀብት አንድ በአንድ ቆጥሮ አስረክቦ ወደሚሄድበት ይሂድ! መልካም የአገልግሎት ዘመን እንመኝለታለን!

~by Bekele Gerba.


“A country where warlord and genocider is praised and its statue built. Any party to come to power in election must promise to remove such statues and signatures from the palace, from the face of Oromiyaa. As the PM Abiy renovated it, the next leader will also have to renovate it. Why should we ”compromise”? Do Jews compromise if statue of Hitler is built in Tel Aviv? This is unacceptable. We should compromise on things that are right, not wrong things that should be condemned by all parties” Biyya Oromiyaa
#AbiyAhmed

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.