ስለ “ስምምነቱ” ግልፅ መሆን ያለባቸው ጉዳዮች ስለ ስምምነቱ መነሳት ያለባቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች አሉ።

ስለ “ስምምነቱ” ግልፅ መሆን ያለባቸው ጉዳዮች

ስለ ስምምነቱ መነሳት ያለባቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች አሉ።

በጠቅላላው፦

1. ውይይቱን ማን ጀመረው? ስብሰባው በማን ተጠራ?

2. አጀንዳው ምንድን ነው? ምንስ ነበር?

3. የውይይቱ ርዕሰ-ጉዳዮች፣ የድርድሩ ነጥቦች ምን ምን ነበሩ?

4. መግባባት የተደረሰባቸው ነጥቦችስ ምንድን ናቸው?

5. ዴሞክራሲያዊ ሽግግሩን የማቀላጠፍ ሥራን አስመልክቶ ምን ግብ አስቀመጡ? ምን ምን ተጨባጭ እርምጃዎች ለመውሰድ ተስማሙ? ምን የጊዜ ሰሌዳ አስቀመጡ?

ምርጫ ቦርድን፣ ፍርድ ቤቱን፣ የሰብአዊ መብት ተቋሙን፣ ሚዲያውን፣ ወዘተ ከአገዛዙና ከአጫፋሪዎቹ ነፃና ገለልተኛ ለማድረግ ምን መግባባት ላይ ደረሱ?

6. የመደራጀት መብትና ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ ተሳትፎ የማድረግ መብትን በእጅጉ የሚገድበውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ሕግ (ለዚያውም ኢዜማ በአንድ ድርጅት–ኢዜማ– ፍላጎት ብቻ የተፃፈ ሕግ) ለማስተካከልና ሕገ-መንግሥታዊ እርምት ለማድረግ ምን የመፍትሄ ሃሳብ አስቀመጡ?

7. የአንድን ብሔር የፖለቲካ የበላይነት ለማስቀጠል እንዲያስችል ሲባል ብቻ፣ አንድ ተመራጭ የአካባቢውን ሕዝብ ቋንቋ እንዲናገር የሚያስገድደውን መስፈርት ሽሮ፣ በራሳቸው ቀዬ በአናሳ ቡድኖች ላይ የአስተዳደር ጫና በመፍጠር permanent minorities የሚያደርገውን ኢ-ሕገመንግስታዊ የምርጫ ሕግ ድንጋጌ በመሞገት፣ ለመቃወምና ለማሰረዝ ምን ሃሳብ አቀረቡ?

አሁን ስላሉ ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተስ፦

1. አሁን በመሬት ላይ ስላሉ ነባራዊ ችግሮች ምን አቋም ወሰዱ? ምንስ የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀመጡ?

በወለጋ፣ በጉጂ፣ በቦረና፣ በድሬዳዋ፣ በቅማንት፣ በወሎ ወዘተ፣መንግሥት (እና በአማራ ክልል ውስጥ በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች፣ በድሬዳዋ ‘ሳተና’ በተባሉ የአብን ቦዘኔዎችና በከተማው ፖሊስ) እየተፈጸመ ስላለው ፍጅት፣ ምን አቋም ወሰዱ? ምን የመፍትሄ ሃሳብ አስቀመጡ?

በሲዳማ ክልል ስለደረሰው ፍጅት እና በደቡብ ክልል በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ ስላለው አፈናና የኮማንድ ፖስት አስተዳደር ምን አቋም ወስደው ምን የመፍትሄ ሃሳብ አስቀመጡ?

2. ስለ ተፈናቀሉና ለርሃብና ለችግር ለተጋለጡት በሚሊዮን ስለሚቆጠሩ ሰዎች ሁኔታ ምን አሉ? ምን ዓይነት የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድ ተስማሙ?

3. በተቃውሞ እንቅስቃሴው ወቅት ለተነሱና እስከ ዛሬም ድረስ ላልተመለሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወሰዱ ለማድረግ ምን መግባባት ላይ ደረሱ?

4. በቋንቋ እኩልነት፣ በፊንፊኔ ወሰን አለመስፋፋትና በ1983 ወሰኑ ላይ ስለመገደቡ ጉዳይ፣ በሕገመንግሥታዊው “ልዩ ጥቅም” አከባበር ሁኔታ ላይ፣ ህገ-መንግሥታዊ የቡድኖች መብትን በማስከበር ጉዳይ፣ የክልልነትና በየደረጃው እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን በሚመለከት ጉዳይ፣ ወዘተ ምን የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድ ተስማሙ?

5. ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማድረግ፣ የድሃውን፣ የሥራ አጦችን፣ የቤትና መሬት የለሽ ምንዱባንን፣ “የልማት ተነሺዎችን” ችግርና ጥያቄ በወቅታዊነትና ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ምን ዓይነት እርምጃዎች ላይ ተስማሙ?

6. በመንግሥት ውስጥ ሌላ መንግሥት ለሆኑ የሙስና መረብ ባለቤቶች፣ ከዚህም የተነሳ ቢሮክራሲውን ሙሉ በሙሉ ለተቆጣጠረው የሙስና አሰራር፣ የምግባር ብልሹነትና የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ምን የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ፣ ምን ተስፋ ሰጪ ተግባር ለመፈጸም፣ ተስማሙ?

7. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሳይቀር ታግዞ፣ የጦር መሳሪያን በነፍስ ወከፍና በቤተሰብ ደረጃ የታጠቀውን ሲቪል ማህበረሰብ (በተለይ በአማራ፣ በፊንፊኔ እና በሌሎች የኦሮሚያና የደቡብ ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ዜጎችን በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ለማጥቃትና ለመፍጀት የሚደራጁትን ወገኖች)፣ ትጥቃቸውን ለማስፈታት፣ በሕግ አግባብ ለመቆጣጠር፣ የኮንትራባንድ የመሳሪያ ሽያችን ለማስቆም ምን እርምጃ እንዲወሰድ፣ ምን ጫና ለማሳደር ተስማሙ?

በአጠቃላይስ የአገሪቱን ፖለቲካ ከብረት ለማላቀቅ ምን አቅጣጫ አስቀመጡ?

8. ከዕለት ወደ ዕለት እየተስፋፋ ያለውን ወንጀል (ዘረፋ፣ ስርቆት፣ ማጭበርበር፣ ወዘተ) ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም ግልጋልቶች (services such as electric power, water, and other utilities) በመደበኛነት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያስችል እርምጃ እንዲወሰድ ለማድረግ ምን መግባባት ላይ ደረሱ?

እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉት የአካሄድ (procedural) እና ይዘታዊ አጀንዳዎች ሳይወያዩ፣ ዝም ብለው “ላለመወቃቀስና ላለመጠላላት” ተስማምተናል እያሉ ከሆነ፣ የዚህ ስምምነት ትርጉም ሊሆን የሚችለው ሁለት ነገር ብቻ ነው፦

1. ጠቅላይ ሚኒስትሩንና በእሱ ሴራ እየተዳከመችና እየከሰመች ያለችውን ኦህዴድ/ኦዴፓን ከደረሰባት የተቀባይነት ማጣት ቀውስ የማዳን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢሬቻ በዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ሊገጥመው የሚችለውን ተቃውሞና ውርደት እንደምንም ለማስቀረት፣ እና በዚህም፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን የማትረፍ ዓላማ ብቻ ያለው አሳፋሪ ተግባር መፈጸማቸውን፤

2. ለዴሞክራሲያዊ ሽግግሩ፣ ለአገሪቱ መረጋጋት፣ ለሕዝቦች ሰላም፣ እና ለዘመናት የሕዝቦች ፖለቲካዊ ጥያቄ ምንም ግድ የሌላቸው፣ ለሕዝብ ሳይሆን ለራሳቸው ህልውናና ስልጣን ብቻ የሚሰሩ፣ እያሉ የሌሉ፣ ድርጅቶች መሆናቸውን።

ከዚህ በመለስ፣ ድርጅቶቹ፣ እነሱም ይታገሉለታል ተብሎ የሚታሰቡትን ታሪካዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች፣ “ኋላቀር (ዘመናዊ ያልሆኑ) እና ትናንሽ ጥያቄዎች” ብሎ ለሚመፃደቅ፣ ለሕዝቦች ጥያቄዎችም ሆነ ለድርጅቶቹ ፍፁም ባዕድ ለሆነና በገሃድ ለሚሰድባቸው ሰው አጨብጭበው መውጣታቸው፣ ታሪካዊ ውርደት ሆኖ ተመዝግቦአል።

እራሳቸውን ከህዝብ ቁጣና ከታሪክ ተጠያቂነት ለማዳን ከፈለጉ፣ እነዚህ ድርጅቶች ሁሉ በአስቸኳይ ለሕዝባቸው ከላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ስለተፈራረሙት ስምምነት ግልፅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ይህን ባያደርጉ፣ ዛሬ ሊያተርፉት የሚሯሯጡለት አብይ ከሳምንታት በኋላ እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ቀርጥፎ እንደሚበላቸው ሊያውቁ ይገባል።

አሁንም ሕዝባዊ ተቃውሞው ይቀጥላል።

ሕዝብ ከግለሰብም፣ ከፓርቲዎችም፣ ከመንግሥትም በላይ ነው።

#Abiy_is_irredeemable #Abiy_must_go#ግባችን_ዴሞክራሲ_እንጂ_አብይ_አይደለም!

1 Comment

  1. In his speech, Abiy was out of touch and far from reality. Not sure whether everyone have heard or understood what he mean by “waan xixiqqoo waggaa soddoma afurtama duraa waan yeroon itti darbe dhiisuu qabna “. What does this means? Does he mean Article 39 from the constitution, the Oromo demands regarding Finfine, Afaan Oromo, self-governance? I think his approach was top-down where he posed his assumptions and expecting that the Oromo people must take, or else he will continue with the genocide. Abiy presents himself like a cyclopedia; he knows everything and can do anything in his power. I am sure he won’t succeed.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.